1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕፃናት ጤና የአፍሪቃ ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥር 10 2005

ከ3,5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት አፍሪቃ ዉስጥ ወባን ጨምሮ ለመከላከል በሚቻሉ በሽታዎች በየዓመቱ ህይወታቸዉ ያልፋል። አዲስ አበባ በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ ለሶስት ቀናት የተካሄደዉ የጨቅላ ሕፃናትን ሞት ማስቀረት ላይ ያተኮረዉ ጉባኤ ሀገራቱ ችግሩን ለማስወገድ በጋራ ለማከናወን የተስማቡበትን አቋም በማሳለፍ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/17N7Z
ምስል AP

ከዚህ ሌላ ጉባኤዉ ለሕፃናት ስለሚያስፈልገዉ የተመጣጠነ ምግብ፤ በሕፃናት ላይ ስለሚፈፀሙ አጓጉል ልማዶችና ድርጊቶችንም በማንሳት ተወያይቷል። ኢትዮጵያ በነጋ እድሜያቸዉ የሚሞቱ ሕፃናትን ቁጥር መቀነስ እንደተሳካላትና ተሞክሮዋንም ማጋራቷ ተገልጿል። ኢትዮጵያ በወቅቱ የአፍሪቃ ሀገሮችን ለማነቃቃትና ለማበረታታት ኃላፊነት ወስዳ የተመለሰች ሲሆን በዚሁ መሠረት ጉባኤዉ ሲካሄድ የየሀገራቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮችን በመጋበዝ ቃል ለማስገባት አዲስ አበባ ላይ መካሄዱንም አመልክተዋል። ጉባኤዉ ላይ እስከትናንትና ድረስ የ27 የአፍሪቃ ሀገራት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች እንዲሁም በህፃናት ጤና ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎቻቸዉን የላኩ በጥቅሉ ሃምሳ የሚሆኑ የአፍሪቃ ሀገሮች ተገኝተዋል። የተመድ እስከ ጎርጎሮሳዊዉ 2015ዓ,ም በሁለት ሶስተኛ መቀነስን በአምዓቱ ግብነት ይዟል። ባለፈዉ ዓመት በብሄራዊ ደረጃ የተካሄደዉ የስነህዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት ዉጤት ኢትዮጵያ ከሚወለዱ አንድ ሺህ ህፃናት መካከል በዓመት አምስተኛ ዓመታቸዉን ሳያከብሩ ህይወታቸዉ ያልፍ የነበረ 217 ሕፃናት ቁጥር ወደ88 ዝቅ ማለቱን አመልክቷል።

Handy Afrika
ምስል Justin Sullivan/Getty Images For The Clinton Foundation

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ