1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 5 2001

ለአለፉት አስራ ስምንት አመታት ኢትዮጽያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ መለስ ዜናዊ በመጭዉ አመት ምርጫ ላለመሳተፍ እና ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸዉ ተሰምቶ ነበር።

https://p.dw.com/p/JcVQ

ባንጻሩ ፓርቲያቸዉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ቢያንስ ለአምስት አመት በስልጣን ላይ እዲቆዩ መወሰኑ ተሰምቶአል። አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸዉ የኤሃዲግ መንግስት ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስልጣን መቆየት አለመቆየት ሁኔታ፣ እየተጫወተዉ ያለ ትያትር ነዉ ሲሉ፣ አስተያየታቸዉን በግልጽ አስቀምጠዋል። የኤህአዴግ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ መወሰኑ ምን ስጋት ቢገጠዉ ነዉ? አዜብ ታደሰ የፖለቲካ ተንታኙን አቶ ዩሱፍ ያሲንን አነጋግራቸዉ ነበር

አዜብ ታደሰ/ሂሩት መለሰ