1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመምህራን አቤቱታ በድሬደዋ

ረቡዕ፣ ጥር 25 2003

የድሬደዋ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት መምህራን የኑሮ ዉድነትን በማገናዘብ የተደረገልን የደሞዝ ጭማሪና የቤት ድጎማ ከእጃችን አልገባም ሲሉ ትናንት ስራ አቁመዉ ተቃዉሞ አሰሙ።

https://p.dw.com/p/Qxhn
ምስል Fotolia/Lorelyn Medina

ጭማሪዉ ከተደረገ ሰባት ወር እንደሞላዉ የሚናገሩት መምህራን ጉዳያቸዉን ወደሚመለከታቸዉ አካላት በመሄድ አቤት እንዳሉ ተናግረዋል። ትናንት ስራአቁመዉ አቤቱታቸዉን ቢያሰሙም መምህራኑ ዛሬ ወደስራ ገበታቸዉ እንዲመለሱ አስተዳደሩ ባሳሰበዉ መሰረት መመለሳቸዉ ተነግሯል።

ዮሃንስ ገብረ እግዚአብሄር

ሸዋዬ ለገሠ