1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመረሃይተ መንግስቷ የዘመን መቀየርያ ንግግር

ሰኞ፣ ጥር 4 2001

ዉድ ያገሪ ዜጎች አሮጌዉን አመት ሸኝተን አዲሱን ስንቀበል ጠቃሚዉንና አስፈላጊ የሆነዉን ነገር ከማያስፈልገን ነገር መለየት ይኖርብናል። በምናጠናቅቀዉ አመት ምን አስፈለጊ ነገር? ምን አይነት ጠንካራ ምኞትስ ነበረን? ስለአንድ ስለምንወደዉ ሰዉ በህይወት መቆየት እናስብ ነበር? ልጅ መወለድ ሃሳብ ነበረን?

https://p.dw.com/p/GWie
አንጌላ ሜርክልምስል AP

ወደፊት ስለምትሰረት ስራ ? ወይንስ ከቤተሰብ እና ከ ጓደኞቻቹ ጋር ያሳለፋቹት ግዜ? ወይም በሰላም እና ደህንነቱ በተሟላ ሁኔታ በመኖራችን ምን አይነት እድል እንዳለን መለስ ብለን አይተናል? ለምሳሌ በመካከለኛዉ ምስራቅ ያለዉን በርካታ ክስተቶች መጥቀስ እንችላለን። በአሁኑ ሰአትም አዲስ ቀዉስ መከሰቱን እናያለን። የሚያስከትለዉን እና እየደረሰ ያለዉን ጉዳት መርሳት የለብንም። ሃማስ እያደረሰ ያለዉ ሽብር አንቀበልም። በሌላ በኩሉ በእስራኤልም ሆነ በፍልስጤም የሚኖሩ ህዝቦች በሰላም እና በአንድ ላይ ለመኖር ምንም አይነት ምንም አይነት አማራጭ አለማግኘታቸዉን መዘንጋት የለብንም። ስለዚህም መንግስታችን ሊረዳ በሚችለዉ ሁሉ እርዳታችንን መስጠት እንፈልጋለን።