1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመረሳት ዕጣ የገጠመው የኮት ዲቯር ውዝግብ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 10 2003

በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ኮት ዲቯር ባለፈው ህዳር ወር ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊው ምርጫ በኋላ በአሸናፊው እና በተሸናፊው ፕሬዚደንቶች አላሳ ዋታራ እና ሎውሮ ባግቦ ደጋፊዎች መካከል የቀጠለው ግጭት አሁን ሀገሪቱን ወደርስበርሱ ጦርነት እያመራት ይገኛል።

https://p.dw.com/p/RAfw
ምስል AP

የዋታራ ደጋፊዎች ባለፈው ሰኞ በምዕራብ የሀገሪቱ ከፊል የምትገኘውን ከአቢዦ እና ከቡዋኬ ቀጥላ ትልቋ የሆነችውን የቱሌፕለ ከተማን ተቆጣጥረዋል። ከሁለት ቀናትም በፊት ብዙ የዋታራ ደጋፊዎች በሚገኙበት የአቦቦ ሰፈር አቅራቢያ ባለው በደራ የአቢዦ የማርሌይ ሰፈር በሚገኘው የሲያካ ኮኔ የገበያ ቦታ በተጣለ የፈንጂ ጥቃት ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል።

አርያም ተክሌ