1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመሬት ቅርምትና ድሃ ሀገራት

ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2003

በበርሊን የተካሄደ ዓለም ዓቀፍ መድረክ ለዓለም ህዝብ ዳቦ የለም፤ የመሬት ቅርምት በድሃ ሀገራት በሚል ከተለያዩ ሀገራት የተጋበዙ ተናጋሪዎችን አስተናግዷል።

https://p.dw.com/p/RNYH
ምስል picture alliance/dpa

ጉባኤዉን በንግግር የከፈቱት የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ በምግብ እጥረት በሚቸገሩ አገሮች የዉጭ አገር ቱጃሮች መሬት በሊዝ ገዝተዉ እህል ማምረት መጀመራቸዉ ዉሎ አድሮ ለማኅበረሰቡ ችግር እንደሚሆን አሳስበዋል። የዉጭ ምንዛሬ ለማግኘትና ለዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር በሚል ለባለሃብቶቹ ከሚሰጠዉ መሬት የሚፈናቀለዉ ማኅበረሰብም በጉዳዩ ቅሬታ እንዳለዉ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። ዉይይቱን የተከታተለዉ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ሁኔታዉን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ስላለዉ፤ በመድረኩ ተገኝተዉ ንግግር ካደረጉት ተጋባዦች አንዱ የሆኑትን ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ኃላፊን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሠ