1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንና ያልሠመረው ሽምግልና፣

ሰኞ፣ ግንቦት 15 2003

ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህ፣ ከሥልጣን መንበር ከወረዱ ፤ የመን በእርስ-በርስ ጦርነት እንደምትማቅቅና የአል ቓኢዳ መፈንጫ እንደምትሆን ከመለፈፍ ካለመቦዘናቸውም፤

https://p.dw.com/p/RPZA
ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህን የሚቃወም የህዝብ ሰልፍ፣ በሰንዓ፣ምስል DW

አሁንም ለ 3ኛ ጊዜ ሽምግልናው እንዳይሠምር አደናቅፈውታል። በተባበረው የዐረብ አሚሮች ኅብረት ኤምባሲ ቅጽር ግቢ የተጠበቀው የዕርቀ ሰላም ስምምነት ሳይሳካ ቀርቷል። የባህር ሰላጤው አገሮች ፤ አደራዳሪው ተወካይ፣ እንዲሁም የአሜሪካና የአውሮፓ አምባሳደሮች በቦታው ተገኝተው ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳሌህን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ፤ የታጠቁ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ለ 2 ሰዓት መፈናፈኛ አሳጥተው እንደነበረ ተመልክቷል። ዝርዝሩን ነቢዩ ሲራክ

ነቢዩ ሲራክ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ