1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንግሥት እርምጃና የሙስሊሙ ሰላማዊ ተቃውሞ፣

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 25 2004

ጉዳዩ አያሌ ወራት የወሰደ መሆኑን የሚናገሩ አሉ። ባለፈው ዓርብ ግን ፣ የሰዎች ህይወት እስኪቀጠፍ የኃይል እርምጃ የተወሰደበት ሁኔታ መከሠቱ በወቅቱ የተገለጠ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፣ ከመደበኛው የእስልምና ሃይማኖት ለየት ያለ፤

https://p.dw.com/p/14pL0
***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B
Karte Äthiopien englisch

ጉዳዩ አያሌ ወራት የወሰደ መሆኑን የሚናገሩ አሉ። ባለፈው ዓርብ ግን ፣ የሰዎች ህይወት እስኪቀጠፍ የኃይል እርምጃ የተወሰደበት ሁኔታ መከሠቱ በወቅቱ የተገለጠ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያውን ሙስሊሞች፣ ከመደበኛው የእስልምና ሃይማኖት ለየት ያለ፤ አህባሺዝም የተባለ አዲስ ሃይማኖታዊ ትምህርት በግዴታ እየተጫነብን ነው። የአገሪቱ የእስልምና ከፍተኛ አመራር፣ ያላንዳች ተጽእኖ በነጻ ይመረጥ! የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎች አቅርበው መልስ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ሙስሊሙ ማኅበረሰብ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ በማቅረብ ላይ ስላለው ጥያቄ መገናኛ ብዙኀን አብራርተው አላቀረቡም በማለት ትናንት በ SMS የደረሱንን መልእክቶች ማሰማታችን ይታወስ ይሆናል። በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን በቃል ስሞታ ያቀረቡ አድማጮችም አሉ። ከአዲስ አበባና ከጎንደር ፣ ሁለት ሙስሊሞች የሰጡትን አስተያየት ቀጥሎ እናቀርባለን።

ድምፅ

የህዝብ አስተያየት

መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይግባ ለሚለው የሙስሊሞች ጥያቄ፣ በፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር፤ የፌደራሊዝም ሥርዓትና የመንግሥታት ግንኙነት መጠናከር ዋና ስራ መሪ(ዳይሬክተር) አቶ እውነቱ ብላታ ደባላ መልስ ሰጥተዋል።

ድምፅ

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ