1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመኢአድና የአንድነት አቤቱታ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 1 2006

መኢአድ ባለፈው ዓመት ሐምሌ 2005 ዓም ከ600 ጠቅላላ አባላቱ 390ው በተገኙበት ስስበባ ቢያካሂድም ምርጫ ቦርድ ግን ምልዐተ ጉባኤው አልተሟላም ሲል መዋሃድ እንደማይችሉ ማሳወቁን የአመራር አባላቱተናግረዋል ።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉባኤ ሲያካሂድ የተገኙት 285 አባላት በመሆናቸው ይህ ሕጋዊ እንዳልሆነ በፅሁፍ ማሳወቁን ገልጿል ።

https://p.dw.com/p/1Cr00
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍርትህ ፓርቲ ውህደታችን እንዳይሳካ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንቅፋት ሆኖብናል ሲሉ አማረሩ ።መኢአድ ባለፈው ዓመት ሐምሌ 2005 ዓም ከ600 ጠቅላላ አባላቱ 390ው በተገኙበት ስስበባ ቢያካሂድም ምርጫ ቦርድ ግን ምልዐተ ጉባኤው አልተሟላም ሲል መዋሃድ እንደማይችሉ ማሳወቁን የአመራር አባላቱ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል ።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ፓርቲው ጉባኤ ሲያካሂድ የተገኙት 285 አባላት በመሆናቸው ይህ ሃጋዊ እንዳልሆነ በወቅቱ በፅሁፍ ማሳወቁን ገልጿል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ