1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስቶክሆልም የመኪና ግጭት ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

እሑድ፣ ሚያዝያ 1 2009

ስዊድን ርዕሠ-ከተማ ስቶክሆልም ዉስጥ ማንነቱ በዉል ያልተነገረ ግለሰብ አንድ የጭነት መኪናን ከትልቅ የገበያ አዳራሽ ጋር አላትሞ በትንሹ ሦስት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች አምስት ቆሰሉ።የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች የሟቾቹ ቁጥር እስከ አምስት እንደሚደርስ ቢዘግቡም የከተማይቱ ፖሊስ ግን ከሦስት በላይ ሰዉ መሞቱን አላረጋገጠም።

https://p.dw.com/p/2atXG
Schweden Stockholm LKW fährt in Menschenmenge - DW-Bild
ምስል DW/N. Startseva

Q&A _Stockholm- Lkw rast in Menschenmenge - MP3-Stereo

 

አርብ ከቀትር በኋላ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ በሚገኝ የገበያ ማዕከል በአነስተኛ የጭነት መኪና ሆነ ተብሎ በተፈፀመ ግጭት ቢያንስ የሦስት ሰዎች ህይወት ጠፋ ። በርካታ የንግድ መደብሮች በሚገኙበት እና ገበያተኞችም በሚንቀሳቀሱበት በዚሁ ቦታ በደረሰው አደጋ በርካቶችም መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።  ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ  የተኩስ ልዉዉጥ መሰማቱን የዓይን እማኞች ተናግረዋል ። አደጋው የሽብር ጥቃት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል ። ፖሊስ እስካሁን አንድ ተጠርጣሪ መያዙ ተገልጿል። ለጥቃቱ  እስካሁን ማንም ኃላፊነት አልወሰደም። ከአደጋው በኋላ የምድር ውስጥ ባቡሮች አገልግሎት ተቋርጧል ። የከተማዋ ቲያትር እና ፊልም ቤቶች ተዘግተዋል። የአውሮጳ መንግሥታት ጥቃቱን በማውገዝ ለስዊድን ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ