1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመዠንገር ደን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 3 2002

አፍሪቃ በኢንዱስትሪ ያደጉት ሀገራት የህግ አዉጪዎች ላደረሱት ብክለት ከሚከፍሉት ካሳ በተጨማሪ የአደገኛ ጋዞችን ልቀት መጠን በመቀነሱ ላይ መስማማት እንደሚኖርባቸዉ አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/K5Qq
ብክለትን ለማፅዳት ደንን ማልማትምስል AP

የዝግጅቱ ጉባኤ በተጠናቀቀበት ወቅት በወጣዉ የጋራ መግለጫም ያደጉት ሀገራት ቢያንስ በአዉሮጳዉያኑ 2020ዓ,ም ብክለቱን ወደ40በመቶ እንዲቀንሱ ተጠይቋል። ከዚህ በተጨማሪም አፍሪቃ የካርቦን ንግድ በሚሉት ስልትም ንቁ ድርሻ እንዲኖራት ታልሟል። ይህ ስልት በኢንዱስትሪ የበለፀጉት መንግስታት ወደከባቢ አየር የሚለቁትን አደገኛ ጋዝ መጠዉ የሚያስቀሩ ደኖችን መትከልና ያሉትን መጠበቅን ይመለከታል። በዓለም ዙሪያ ይህን የሚያንቀሳቅሱ 1,600 ፕሮጀክቶች ሲኖሩ በአፍሪቃ የሚገኙት 30ብቻ ናቸዉ። ከእነሱም 15ቱ በደቡብ አፍሪቃ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸዉ ተመልክቷል። ዣን ፒንግ በዚህ ረገድ ክፍለ ዓለማቸዉ የታመቀ አቅም እንዳላት ነዉ የተናገሩት። የዓለም ባንክ ወደከባቢ አየር አንድ ሶስተኛ እጅ የአደገኛ ጋዝ መጠን ቢለቀቅ በአዳጊ ሀገራት የሚያደርሰዉ ጉዳት 80በመቶ እንደሚሆን ይገምታል። የቡርኪናፋሶ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሳልፎዉ ሳዋዶጎ አፍሪቃ እንዲህ ያለዉን የአየር ጠባይ ለዉጥ ያስከተለባትን መዘዝ ለመቋቋም 44 ቢሊዮን ዩሮ ያስፈልጋታል ብለዋል። ከባቢ አየርን ከብክለት በማፅዳትም ሆነ የአየር ርጥበት ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ደን የሚሰጠዉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ