1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመድሃኒት አወሳሰድ ጥንቃቄ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2004

ፀረ- ባክቴሪያ ወይም በባለሙያዎች አንቲባዮቲክ በመባል የሚታወቁት መድሃኒቶች አወሳሰድ ጥንቃቄ እንደሚያያሻዉ የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ። እንዲህ ያለዉ መድሃኒት ከታዘዘበት ወቅት እና መጠን አንሶ ከተወሰደ እንዲያጠፋቸዉ የታለመላቸዉ፤

https://p.dw.com/p/14rwD
ምስል picture-alliance


ባክቴሪዎች ፀራቸዉን ይለምዱትና በመድሃኒቱ መፈወስ ያቅታል። የዕለቱ ጤናና አካባቢ መሰናዶ ባለሙያ በማነጋገር ትኩረቱን እዚህ ላይ አድርጓል። መድሃኒት ስለሚላመድ የበሽታ ሁኔታ በተደጋጋሚ ይነገራል። እዚህ ጀርመን ቤርጊሽግላድባህ በተሰኘች ከተማ ማሪየን ሆስፒታል የሚሰሩት የአጥንትና ጠቅላላ ህክምና ባለሙያ ዶክተር ንጉሤ በቀለ በተለይ አንቲባዮቲክ በመባል ስለሚታወቁ መድሃኒቶች አወሳሰድና ሊደረግ ስለሚገባዉ ጥንቃቄ ማብራሪያ ሰጥተዉናል። ሃኪሞች መድሃኒትን ሲያዙ የተወሰነለትን የጊዜ ገደብ ጠብቆ አለመዉሰድ ሊያስከትል ስለሚችለዉ ችግርም ባለሙያዉ አብራርተዉልናል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ