1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጀመርያ ቀን በትምህርት ቤት

ሐሙስ፣ መስከረም 6 2003

በጀርመን የበጋዉ ወራት የአረፍት ግዜ አልቆ ትምህርት ቤቶች ከጀመሩ ሳምታትን አስቆጥረዋል። በተለያዩ የጀርመን ፊደራል ክፍላተ ሃገራትም የትምህርት መጀመርያዉ ግዜ እና የእረፍት ግዜ እንደየ ክፍለ ሃገራቱ መረሃ ግብር ይለያያል።

https://p.dw.com/p/PDoQ
ምስል AP

የነገ ተስፋ የሆኑት ህጻናት የእዉቀት ገበያ የሆነዉን ትምህርት ቤት ለመጀመርያ ግዜ ሲረግጡ የህይወትን አዲስ ምእራፍ ሲጀምሩ በከፍተኛ ድግስ እና ባህላዊ ስርአት ነዉ። እዚህ ራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በቦን ከተማ ባለ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት መጀመርያ ስርአትን ተመልክተናል፣ በሌላ በኩል በሌሎች ትምህርት ቤቶች ልጆቻቸዉን ለእዉቀት ገባያ ያበቁ ኢትዮጽያዉያንን የጀርመናዉያን የትምህርት ቤት አጀማመር ባህልን እንዲያወያዩን ጋብዘናል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ።

የነገ አገር ተረካቢ የሆኑት እና ለአዲሱ አለም እንግዳ የሆኑትን ህጻናት ከተፈጥሮ ለማስተዋወቅ ታላላቆች ያላቸዉን እዉቀት፣ ያሳለፉትን የኑሮ ዉጣ ዉረድ፣ የሚያሳዩበት፣ የሚያስተምሩበት የትዉልድ ርክክብ መሰት ትምህርት ቤት ነዉ። በጀርመን አገር ማንኛዉም ከ 5-7 አመት እድሜ ላይ የሚገኝ ህጻን የአንደኛ ክፍል ትምህርት ይጀምራል። የትምህርት ቤት መሄጃዉ እድሜ ቢለያይም በበዛ ቢበዛ በሰባት አመቱ ትምህርት ቤት መጀመር ይኖርበታል። ወላጆችም በልጃቸዉ ትምህርትቤት መግባት ወይም መጀመር አለመጀመር ተጠያቂ ናቸዉ።

በኖርዝራይን ዊስት የበጋዉ እረፍት ግዜ ተጠናቆ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጀመርያዎቹን ማለት የአንደኛ ክፍል ተማሪዎችን እንኳን ለዚህ ምእራፍ አደረሳችሁ በማለት በሮቻቸዉን ከፍተዉ በደማቅ ተቀብለዋቸዋል። በዚህ የትምህርት መጀመረቅት የሚጀምሩትን የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ባለፈዉ አመት ማለት የሁለተኛ እና የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ሲሉ መዝሙር በመዘመር የትምህርት ቤቱን ግቢ የመጫወቻ ቦታ እንዲሁም አንዳንድ እነሱ የተማሩትን የትምህርት ቤት ህግጋት በመግለጽ ይቀበሉዋቸዋል። እዚህ በቦን ከተማ ያለዉ የኤሪክ ኬስትነር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት ትምህርት ቤቱ ከተለያዩ ክፍለ አለማት የመጡ ተማሪዎችን እንደተቀበለ ይገልጻሉ።
በትህርት ቤት አጀማመር ስነ-ስርአቱ በመጀመርያ ቤተ ክርስትያን ሄዶ የጸሎት ስነ-ስነስርአት መካፈል፣ በባረክ ይሆናል። ግን ትምህርት ቤት ከመጀመር በፊት ህጻኑ ለህክምና ወደ ሃኪም ጋር ሄዶ ለትምህርት ብቁ መሆኑን መመርመር አለበት፣ ዝርዝሩን ያድምጡ!

Einschulung in Brandenburg
ምስል picture-alliance/ ZB

አዜብ ታደሰ፣ ነጋሽ መሃመድ