1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመገናኛ ብዙኃን ም/ቤት ምስርታ

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ጥር 10 2008

ወደ 10 ዓመት ወስደዋል የተባለዉ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ጥር 3 2008 መቋቋሙ ይፋ መሆኑ ይታወቃል። ይህም ምክር ቤት አገሪቱ ዉስጥ ያሉትን የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞችን የሚያስተዳድር ሲሆን የሚዲያ ኢንዱስትሪዉ የምያጋጥሙት ችግሮች መፍቴ እንደሚሆንለትም ይነገራል።

https://p.dw.com/p/1Hg6T
Äthiopien Addis Abeba Medienrat
ምስል DW/G. T. Hailegirorgis

[No title]

በተለይም አገሪቱ ዉስጥ የሚሰሩ የግል የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሆኑ ጋዝጠኞች በመንግስት በኩል የሚደርስባቸዉ ሳንሱር ማለት ቅድመ ምርመራ የማድረግ ፣ዛቻ፣ የአካል ጥቃት፣ ካዛም አልፎ ለእስር እንደሚዳረጉ የሚድያ መብት ተከራካርዎች በሚያወጡት ዘገባዎች ያሳያሉ። ስለዚህም ነዉ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ማቋቋሙ ማፈናፈኛ ላጡት ተቋማትም ሆነ ለጋዜጠኞች መፍትሄ ይሆናል የተባለዉ።


ይሁን እንጅ ይህን ምክር ቤት መቋቋሙን ተከትሎ «ሁሉ አቀፍ» ምክር ቤት አይደለም ሲሉ ቅሬታቸዉን የሚያሰሙም አልጠፉም። አገሪቱ ዉስጥ ካሉት የምድያ ተቋማት ግማሽ ያህሉ በምስረታዉ ላይ እንዳልተሳተፉም የሚድያ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ወንደሰን ተሾመ የምክር ቤቱን ምስረታ ትልቅ ስኬት ነዉ ካሉ በኋላ በምስረታዉ ግዜ «በአካሄዱ» ላይ እንዳልተስማሙ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። በተካሄደዉም የምክር ቤት ምርጫ 200 መረጮች ይገኙበታል ተብሎ ቢጠቀስም 40 ሰዉ ብቻ እንደተገኘ እና ከዚህም መካከል 18 ሰዉ ብቻ ድምፅ እንደሰጠ ገልፀዋል።


ሌላዉ ጉዳይ ይላሉ አቶ ወንደሰን፣ ለምክር ቤቱ የሚዉለዉ የገንዘብ ምንጭ መንግስት በዴሞክራሲ ፉንድ በሚባለዉ ልያግዝ ፍላጎቱን ብያሳይም እሄን አንቀበልም ስላሉ፣ የገንዘብ ምንጩ ከየት እንደምመጣ አይታወቅም ወይም ግልፅ አይደለም ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይህ መንግስት ካያወጣዉ አዲሱ ሕግ ጋር እንደምፃረር እና እሳቸዉም እንዳልተቀበሉት ተናግረዋል።

አገሪቱ ዉስጥ ያሉት የሚዲያ ዘገባዎች እንደምያመለክቱት፣ በተመረጡት የምክር ቤቱ አመራሮች እምነት የለንም እያሉ አስተያየተቸዉን አስነብበዋል፣ ምክንያቱም ግለሰቦቹ የግላቸዉን ፍላጎት ልያሰፈፅሙ ስለሚችሉ ብለዉም ጠቅሰዋል። ስለዚህም በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ከየትኛውም ተፅዕኖ ነፃ እና ገለልተኛ የሆነ ም/ቤት ለመምስረት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንን አቶ ወንደወሰን አብራርተዋል።

Karte Äthiopien englisch


«አጀንዳችን ተነጥቀናል» የሚሉት አቶ ወንደወሰን አንድ ጋዜጤኛ ችግር ብያጋጥመዉ የሚከሰሰዉ እራሱ ነዉ እንጅ ባሌቤቶቹ ስላል ሆኑ ምክር ቤቱ ጋዜጠኞችን ማሳተፍ እንዳሌለበት ያሳስባሉ። ምክር ቤቱ ከነ ችግሩ መቋቋሙ ትልቅ ነገር ነዉ ሲሉ በማህበራዊ ደረ-ገፅ ያደረግነዉ ዉይይት ተሳታፍዎች አሰተያየተቸዉን አጋርተዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሀሳብን በነፃ የማይግለፅበት አገር ዉስጥ ምክር ቤቱ መቋቋሙ ብዙም ፋይዳ የለዉም ስሉ ተከራክረዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታዴሴ