1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጠን ያለፈ የአየር ንብረትና ለዉጡ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 26 2003

አዲሱን የአዉሮጳዉያን ዓመት 2011ን የዘመን ቀመራችን ብሎ ዓለም በርችት ተኩስና በልዩልዩ ፈንጠዝያ ሲቀበለዉ፤

https://p.dw.com/p/Qn8r
ከባድ ዝናብና ማዕበል አስከታዩ ደመናምስል picture alliance / dpa

በተፈጥሮ ረገድ፤ አዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ በበረዶ፤ አዉስትራሊያና ብራዚል በጎርፍ፤ ፊሊፒንስ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ የመሬት መንሸራተት አንድ ብሎ ሥራዉን ጀምሯል። በተለያዩ አካባቢዎች የምናስተዉለዉ ከመጠን ያለፈ የሚባለዉ የአየር ጠባይ ሁኔታ ዓለም ከሚነጋገርበት የአየር ንብረት ለዉጥ ጋ ግንኙነቱ ምን ያህል ነዉ። የአየር ጠባይ ትንበያን ለማመን የሚያዳግታቸዉ ወገኖች እንዳሉ ሁሉ የየዕለቷን ትንቢት ተንተርሰዉ የሚንቀሳቀሱም ሞልተዋል። ክረምት ከበጋ የአለባበስ ስልቱ በማይቀያየር አካባቢ ለሚኖረዉ ኅብረተሰብ ዕለታዊዉ የአየር ጠባይ ትንበያ ብዙም ባላስጨንቀዉ፤ ለአዉሮጳና መሰል አካባቢ ኗሪዎች ግን ዋጋዉ ትልቅ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በዚህ ረገድ ብዙ ብዙ ይባላል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ