1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙሥሊሞች እና የፖሊስ ግጭት በአርሲ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2004

የኦሮሙያ ፖሊስ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ በምዕራብ አርሲ ልዩ ስሙ አሳሳ በተባለ አካባቢ በአክራሪነት ጸርጥሮ ባሰራቸው በአንድ ያካባቢው ኢማሙ ደጋፊዎች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት አሥር ፖሊሶች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የኦሮሙያ ፖሊስ ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/14neB
This mini mosque shares space inside a tree, in Harar, Ethiopia July 21, 2007. For 1,000 years, this city on a hilltop has been a center of Islamic faith in the Horn of Africa, with a forbidding, 4-meter (13-foot) wall surrounding ancient mosques and serpentine alleyways. Harar was named a UNESCO World Heritage site last year, joining some of the world's top landmarks such as the Grand Canyon in the United States, the Great Wall of China and the Acropolis in Greece. It is also the fourth holiest city in Islam _ behind Mecca, Medina and Jerusalem (AP Photo/Anita Powell)
ምስል AP

የኦሮሙያ ፖሊስ ኮሚሽን ለግጭቱ መንሥዔ ናቸው የተባሉት ኢማም በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ሙሥሊሞችን ለጦርነት ቀስቅሰዋል በማለት ይወነጅላል። በምዕራብ አርሲ ስለታየው ግጭት የአዲስ አበባ ወኪላችን ታደሰ እንግዳው የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማልን አነጋግሮዋል፤ አቶ ሽመልስ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች ሙሥሊሞች አነሱት ስለተባለው ተቃውሞ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመግለጽ፡ ስለ ምዕራብ አርሲው ግጭት ግን ለዶይቸ ቬለ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ታደሰ እንግዳው

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ