1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙሲሊም ኢትዮጵያዉያን አቤቱታ

ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2005

የኢትዮጵያ ሙሲልም ምዕመናን በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት መንግስት ሰዎችን ማሰሩን መቀጠሉን፦ እስር ላይ የሚገኙትንም ፍርድ ቤት በነፃ ሲያሰናብት ፖሊስ አለቀቀም ማለቱን ለዶቼ ቬለ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/16k8C
ምስል DW/Tedla Getachew

ዓለም ዓቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽና እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የሃይማኖት ነፃነት ተመልካች መድረክ ባለፈዉ ሳምንት በተከተታትይ ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱንና ይፋ አድርገዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽ፦ የኢትዮጵያ መንግስት የቀጠለዉን የሙስሊም ተቃዉሞ ለመግታት በሚወስደዉ የኃይል ርምጃ የሰብዓዊ መብቶችን እየጣሰ ነዉ ሲል በዘገባዉ አመልክቷል። የመንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ በርካታቶች መታሠራቸዉን፤ አሁን አብዛኞቹ እስር ላይ እንደሚገኙም ድርጅቱ ጠቅሷል።

Logo Amnesty International

የአምነስቲ ዘገባ ፖሊስ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሟቸዉን በሚያገልፁ ወገኖች ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል ርምጃ መጠቀሙንም ገልጿል። የዩናይትድ ስቴትስ የሃይማኖት ነፃነት ተመልካች መድረክ በበኩሉ መንግስት  በሙስሊም አማኞች ላይ ቁጥጥሩን አጥብቋል ሲል ከሷል።የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን USCIRF በዘገባዉ የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሟቸዉን ያሰሙ ሙስሊሞችን አስሯል፤ 29ኙን ደግሞ ባለፈዉ ሰሞን በአሸባሪነት ወንጅል ከሷል ሲልም አመልክቷል።

የመብት ተማጋቾቹ ዘገባ ይፋ ከሆነ በኋላ የከሚሴ ኗሪ መሆናቸዉን የገለፁ አንድ አድማጭ ለዶቼ ቬለ በላኩት መልዕክት እንዳመለከቱት በአካባቢያቸዉ ቤቶች እየተፈተሹ አሁንም ሰዎችም ይታሰራሉ። ወደአካባቢዉ ደዉለን ለማረጋገጥ ስንሞክር የእሳቸዉ የስልክ መስመር ባይሳካልንም ደቡብ ወሎ የሚገኙ አንድ ሌላ ኗሪ በሃይማኖታች ጣልቃ ይገባል ያሉት መንግስት ኃይሎች በአካባቢያቸዉ ይፈፅማሉ ያሉትን እንዲህ ገልፀዉልናል። እሳቸዉ እንደሚሉት ከሌሎች ስፍራ የተያዙ ሰዎች ወደእነሱ አካባቢ ተወስደዉ ይታሰራሉ፤ ከዚያም የት እንደሆነ ወዳልጠቀሱት ወደሌላ ስፍራ ይወሰዳሉ። ሌላዉ ኤሎባቡር የሚኖሩ የሃይማኖቱ ተከታይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸዉ እስራት እየተካሄደ ባይሆንም ከዚህ በፊት የታሠሩትን ፍርድ ቤት በነፃ ቢያሰናብትም ፖሊስ አልለቀቃቸዉም ይላሉ፤

Karte Äthiopien englisch

ሥለ ጉዳዩ የመንግስት ቃል አቀባይን በስልክ  ለማነጋገር ያደረግ ነዉ ሙከራ ለጊዜዉ አልተሳካም።ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት መንግስት የአክራሪ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ያሰጋኛል ባይ ነዉ። ባለፉት በርከት ያሉ ወራት መንግስት ሐባሽ የተሰኘዉ የእስልምና ሃራጥቃ እምነትን ተቀበሉ በሚል አስገድዶናል፤ የእስልማና ምክርቤትን ተጠሪዎች በመምረጥ ሂደት ደጋፊዎቹን ለማስመረጥ ጣልቃ ገብቷል በሚል ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ እያካሄዱ እንደሆነ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠቅሷል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ