1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት

ረቡዕ፣ መጋቢት 24 2006

ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል

https://p.dw.com/p/1BaLQ
ምስል picture-alliance/dpa

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተከሰሱ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎችን የተከሳሽነት ቃል መቀበሉን ዛሬም ቀጥሎ ዉሏል።ቃሊት ያስቻለዉ የፍርድ ቤቱ አራተኛ መደበኛ ችሎት ትናንት የአንደኛ ተከሳሽ የአቡበከር አሕመድን ቃል አድምጦ ነበር።ዛሬ ደግሞ የሁለተኛ እና የሰወስተኛ ተከሳሾችን ቃል አድምጦ የተቀሩትን ተከሳሾች ቃል ለማድመጥ ለነገ-ቀጠሮ ሠጥቷል።ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የችሎቱን የዛሬ ዉሉ ተከታትሎት ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ