1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙዩኒኩ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባዔ

ዓርብ፣ ጥር 29 2007

በዛሬው ዕለት በደቡብ ጀርመን ርእሰ ከተማ ሙዑንሸን(ሙዩኒክ) ለተከፈተው ጉባዔ መላው ዓለም ዐቢይ ግምት ሰጥቶታል። ለዚህም በቂና አንገብጋቢ ምክንያት አለው። ጸጥታ ተመልካቹ ጉባዔ ፣ ለዋና ዋና አወዛጋቢ ጉዳዮች ፣ በስብሰባው ወቅት ፥ አለያም ከዚያ

https://p.dw.com/p/1EXRY
ምስል DW/A. Feilcke

በኋላ አዲስ መፍትኄ ይፈልጋል። በሶሪያና ኢራቅ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ሲል የሠየመው አሸባሪ ቡድን ተግባር ፤ -----እስካሁን ቁጥራቸው ከ 5,300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበት የምሥራቅ የዩክሬይን ውጊያ ፣ ምክክር ከሚደረግባቸው ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ ናቸው።

20 ርእሳነ ብሔርና መራኅያነ-መንግሥት፤ እንዲሁም 60 የውጭና የመከላከያ ሚንስትሮች በጉባዔው ይሳተፋሉ ፤ በዛ ያሉ የፀጥታ ጉዳይ ባለሙያዎችም ሆኑ ጠበብትም ይገኛሉ። ለስብሰባው የሚቀርቡትን የመወያያ አርእስት በተመለከተ የስብሰባው መሪ ቮልፍጋንግ ኢሺንገር ለዶቸ ቨለ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ላይ አብራርተዋል።

«ውዝግቦች ሲበራከቱና ይበልጥ አሳሳቢ ሲሆኑ፤ ምናልባት ያኔ ይሆናል የሙዩኒኩ የጸጥታ ጉባዔ ይበልጥ አጓጊና መፍትኄ እንዲሹ ለሚወተወቱ መሪዎችም የላቀ ትርጉም የሚኖረው። »

ውዝግቦችን በተመለከተ ፤ የሐሳብ ልውውጥ የሚደረገው፣ ይፋ በሆነው የውይይት መድረክ ብቻ ሳይሆን፤ በሆቴሎች ክፍሎች አካባቢዎች ጭምር ነው።

Der russische Aussenminister Sergej Lavrow auf der 46. Muenchner Sicherheitskonferenz in Muenchen
ምስል AP

እዚህ ላይ ለምሳሌ ያህል የተቃቃሩት የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ እና የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ፤ መገናኘታቸው አይቀሬ ነው። ጉዳዩ ሁለቱን አገሮች ብቻ አይደለም፣ ሩሲያንና ምዕራባውያንንም አቃቅሯል። ይሁንና ባለፉት 10 ወራት ከ 5,300 በላይ ሕዝብ ያለቀበት በኪቭ መንግሥት ወታደሮችና በምሥራቅ ዩክሬይን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ውጊያ በተኩስ አቁም እንዲገታና ለውዝግቡ መፍትኄ እንዲፈለግለት ጥረት ለማድረግ የጀርመን መራኂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ፍርንሷ ዖላንድ ትናንት ከኪቭ መንግሥት ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ ጋር የመከሩ ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ ሞስኮ ውስጥ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ሳይወያዩ አይቀሩም። በመኻሉም ለአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም መደረጉ በመነገር ላይ ነው። የምሥራቅ ዩክሬይን ይዞታ በእንዲህ እንዳለ ነው በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የሙዩኒኩ ጉባዔ በ ቮልፍጋንግ ኢሺንገር የተከፈተው። በዛ ያሉ ልዑካን አስከትለው በጉባዔው የሚሳተፉት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፤ « ሩሲያ ለምታሳየው የጠብ ጫሪነት ባሕርይ አገራቸው አጸፋውን ከፍ ታደርጋለች» ማለታቸውን በደቡብ ጀርመን የሚታተመው ጋዜጣ(ዙድዶይቼ ትሳይቱንግ) ጠቅሷል።

Ukraine Kiew John Kerry und Arsenij Jazenjuk
ምስል picture-alliance/dpa/Sergey Dolzhenko

የጀርመን ፌደራል መንግሥት፣ ለዩክሬይን ውዝግብ በዲፕሎማሲ መላ እንዲገኝለት ካለፈው የፀጥታ ጉባዔ አንስቶ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች።ጀርመን ለዓለም አቀፍ ውዝግቦች እልባት ማግኘት የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ሰፊ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኗ ይነገራል። በሰሜናዊ ው ኢራቅ የሚገኙትን ኩርዳውያን ሚሊሺያ ጦረኞች ጦር መሣሪያ እንዲቀርብላቸው ማድረግ ብቻ ሳይሆን ሥልጠናም ሰጥታለች። የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊ ያን ኤልያሰን---

«ማለት የምችለው፤ ጀርመን ካላት ልምድ በመነሣት ውዝግብን ለማስወገድ ትልቅ ድርሻ ማበርከት ትችላለች። ውዝግቡ በሚያጋጥመበት ጊዜና ከዚያም በኋላ፤ መላ በመሻት ረገድ ጠቃሚ ድርሻ ማበርከት አይሳናትም። ከጀርመናውያን ወዳጆቻችን ጋር በዚህ ጥያቄም ሆነ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንወዳለን። »

እ ጎ አ በ1963 የተጀመረው ፤ ስለ ዓለም ይዞታ የሚመከርበት በአውሮፓ እጅግ ትልቁ የጸጥታ ነክ ጉባዔ ዘንድr ለ 51 ጊዜ ነው የሚካሄደው።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ