1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙጋቤ ጀምበር እየጠለቀች ነዉ።ለዚምባቡዌ ይበጅ ይሆን?

ሰኞ፣ ኅዳር 29 2001

"ሙጋቤ የሚባሉትን ካላደረጉ የዘመ-ሥልጣናቸዉ መሠረት መናድ አለበት"

https://p.dw.com/p/GBhv
የኮሌራ መቅሰፍትምስል AP

ዚምባቡዌያዊዉ እዉቅ ደራሲና ገጣሚ ዳምቡልዞ ማሬችራ በ1978 (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ያሳተሙት መፅሐፋቸዉ፣ የወላጆቻቸዉን አኗኗር፤ የእሳቸዉና የአቻዎቸዉን አስተዳደግ፣ ተስፋ-ራዕይ፣ ይተርካል። ሮዴሽያ ግን በመፅሐፉ ርዕሥ ገለጧት።«የረሐብ ቤት»።ሁሉንም አሉት።ከሞት በመለስ በነበረዉን የብሪታንያ ቅኝ ገዢዎች ግፍ-እየተገፉባት፤ በአረመኔ-እርምጃቸዉ እየተሰቃዩ-ባት ያደጉባት ሐገራቸዉን ዛሬ ቢያይዋት የሚሉትን በርግጥ አናዉቅም።ወገናቸዉ ከቅኝ ገዢዎች ግፍ-ነፃ አወጣንሕ ባሉት፣ ነፃ አዉጡኝ ባላቸዉ ገዢዎቹ እያለቀ፤ ሐገራቸዉ እየዘቀጠች መሆንዋ ግን ሐቅ ነዉ።ሐቅነቱ ነዉ የነማሬችራ-ተስፋ ራዕይ ቅጭቱ።እንዴት ለምን ላፍታ አብረን እንጠይቅ።