1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሊ መፈንቀለ መንግሥትና ተቃዉሞዉ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2004

የጦር ሁንታዉ ባስቸኳይ ሥልጣን እንዲለቅ የሐገሪቱ ሕዝብ በሰልፍ ሲጠይቅ፥ የሰላሳ ስምንት የፖለቲካ ማሕበራት ተጠሪዎች ደግሞ ለጦሩ ድጋፍ እንደማይሰጡ አረጋግጠዋል።የማሊ የመስመር መኮንኖችን መፈንቅለ መንግሥት የተለያዩ መንግሥታትና ማሕበራት እያወገዙት ነዉ

https://p.dw.com/p/14T3l
Renegade Malian soldiers appear on television at the ORTM television studio in Bamako in this March 22, 2012 still image taken from video. Renegade Malian soldiers went on state television on Thursday to declare they had seized power in protest at the government's failure to quell a nomad-led rebellion in the north. REUTERS/Mali TV via Reuters TV (MALI - Tags: POLITICS CIVIL UNREST) THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS. MALI OUT. NO COMMERCIAL OR EDITORIAL SALES IN MALI
ምስል Reuters


የማሊን ፕሬዝዳት የአማዱ ቱማኒ ቱሬን መንግሥት አስወግደዉ ሥልጣን የያዙትን የጦር መኮንኖች የሐገሪቱ ሕዝብና ፖለቲከኞች ተቃወሟችዉ።የጦር ሁንታዉ ባስቸኳይ ሥልጣን እንዲለቅ የሐገሪቱ ሕዝብ በሰልፍ ሲጠይቅ፥ የሰላሳ ስምንት የፖለቲካ ማሕበራት ተጠሪዎች ደግሞ ለጦሩ ድጋፍ እንደሚይሰጡ አረጋግጠዋል።ሻምበል አማዱ ሳንጎ የመሯቸዉ የማሊ የመስመር መኮንኖች ያደረጉትን መፈንቅለ መንግሥት የተለያዩ መንግሥታትና ማሕበራት እያወገዙት ነዉ።የአፍሪቃ ሕብረት ማሊን ከአባልነት ሲያግድ፥ የአዉሮጳ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ ለማሊ የሚሰጡትን ምጣኔ ሐብታዊ ርዳታ አቁመዋል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ