1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማማ አፍሪቃ 75ኛ አመት ክብረ በአል

ሐሙስ፣ መጋቢት 13 1999

ማማ አፍሪቃ በመባል የምትታወቀዋ ደቡብ አፍሪቃዊቷ ታዋቂ ሙዚቀኛ ማሪያም ማኪየባ ሰባ አምስተኛ አመት የልደት በዐልዋን አክብራለች። Pata Pata የተሰኘዉ ዜማዋ እ.አ 1967 በትዉልድ አገሯ በደቡብ አፍሪቃ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን አትርፋበታለች።

https://p.dw.com/p/E0mP
ማርያ ማኬቫ
ማርያ ማኬቫምስል AP

ፓታ ፓታ በተሰኘዉ ሙዚቃዋ በጣም በሚስደንቅ ሁኔታ በአለም ዙርያ በአንድ ግዜ ተደናቂነትን ማትረፉ አስገራሚ ነበር። ትዉልዷን እ.አ የካቲት 25 / 1932 በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ አካባቢ ባለች መንደር እንደሆነ የምትናገረዋ ማርያ ማኪየቫ ፈጣሪዮ በሰጠኝ ስጦታ ትላለች፣ አንድ ግዜ በሰጠችዉ ቃለ ምልልስ ከፈጣሪዩ የተሰጠኝ ተስፈኛነት ቆራጠኝነት እና ማዜም ናቸዉ። በተስፍ እና በቁርጠኝነት በምትቃኛቸዉ ዜማዎችዋ በደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድን በመቃወም እንቅስቃሴዋን ዳር አድርሳለች። ማርያ ማኬቫ በተስፍ በቁርጠኝነት በማዜም በጀመረችዉ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዋ የአፍሪቃዉያን በተለይ የአገሯን ሴት ሙዚቀኞች ወደ መድረክ እንዲወጡ ምሳሌ ሆናለች። በአገራችን በአዲስ አበባ የአሁኑ አፍሪቃ ህብረት የቀድሞዉ የአፍሪቃ ህብረት ድርጅት ጉባኤ ላይ ተገኝታ ፁሁፋን አቅርባለች በተለይ በአራችን ከነበሩት ከታዋቂዎቹ ከያኔዎች መካከል ከሜሪ አርምዴ ጋር ተገናኝታ እንደነበር ይነገራል። የአገራችን የሙዚቃ ንጉስ የጥላሁን ገሰሰን የጥንቱ ትዝ አለኝ የተባለዉን ዜማ በማቀንቀኗ ታዋቂነትን አትርፋለች።