1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማርግሬት ታቸር ምሥጢራዊ ሰነድ

ዓርብ፣ ሐምሌ 17 2007

የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርግሬት ታቸር በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የሚመራዉን መንግሥት ለመጣል ተጠቅመዉበታል የተባለ የከፍተኛዉ ምሥጢር ማስታወሻ ሰነድ በቅርቡ ይፋ ሆነ።

https://p.dw.com/p/1G4KP
EU Großbritannien Premierminister Margaret Thatcher 1984
ምስል Getty Images

[No title]

በተገኘዉ መረጃ መሠረትም በጎርጎሪዮሳዊዉ 1984ዓ,ም ማለትም በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር 1977ዓ,ም በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረዉ እና የሚሊዮን ሕዝብ ሕይወት የቀጠፈዉን አስከፊ ረሀብ ነዉ ለዚህ መሣሪያ ሆኗል። የመንግሥት ምሥጢራዊ ሰነዶች ከሚቀመጡበት የብሄራዊ ሰነዶች ክምችት የመዝገብ ካዝና በዳዉኒንግ ስትሪት ይፋ የሆነዉ የከፍተኛዉ ምሥጢር ማስታወሻ ሰነድ እንደሚያመለክተዉ ማርግሬት ታቸር ለኢትዮጵያ መንግሥት ይሰጥ የነበረዉን እርዳታ ለምዕራቡ ዓለም ባይተዋር እየሆነ የሄደዉን የወታደራዊ መንግሥት ሥልጣን የሚያጠናክር በመሆኑ በወቅቱ ይፋለሙት ለነበሩት ግንባሮች ርዳታዉ እንዲዞርና ሌሎችም ርዳታዎች ለደርግ መንግሥት እንዳይሰጥ ማድረጋቸዉንም ይገልፃል።

ድልነሳ ጌታነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ