1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት

እሑድ፣ መስከረም 29 2009

ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች (Social Media) ከመደበኛዉ መገናኛ ዘዴ ይበልጥ በፍጥነት መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ፤ የግለሰብ፤ የማኅበራት የድርጅቶች አስተያየቶችን በማሰራጨትና ከሁሉም በላይ ሠዎችን እርስ በርስ በማገናኘት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2R2zc
Symbolbild Soziale Netze
ምስል picture-alliance/dpa/Heimken

የማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ሚና እና ኢትዮጵያ

በተቃራኒዉ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዉ አፍራሽ የሚባሉ መልክቶችም የሚተላለፉበት መድረክ ነዉ። ይሁንና የኢንተርኔት አገልግሎቱ ዉስን በሆነበት በኢትዮጵያ መንግሥት ማኅበራዊ መገናኛዉን በተመለከተ የሚያቀርበዉ ክስ የራሱን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመሸፈን ያደረገዉ ርምጃ ነዉ የሚሉ አይደሉም። መንግሥት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ምንጭ የሆነዉን የኢንተርኔት አገልግሎት መክፈት መዝጋቱስ እንዴት ይታያል? የመገናኛ ዘዴዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ በተነሳዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ የሚጫወቱትን አዎንታዊና አሉታዊ ሚና ይዳስሳል።  

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ