1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማአሪ ሠላምና የአዉሮጳ ሕብረት

ዓርብ፣ ጥር 2 2006

።ጄቶዲያ ንጃሚና ቻድ በተደረገዉ የማዕከላዊ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ECCAS) ጉባኤ ላይ ሥልጣን መልቀቃቸዉን ሲያዉጁ፥ የአዉሮጳ ሕብረት ደግሞ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማዝመት ማሰቡ ከብራስልስ ተሰምቷል

https://p.dw.com/p/1Aolt
ምስል picture-alliance/AP Photo


ካለፈዉ መጋቢት ወዲሕ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክን የፕሬዝዳትነት ሥልጣን ይዘዉ የነበሩት የቀድሞዉ የአማፂ ቡድን መሪ ሚሼል ጄቶዲያ ሥልጣናቸዉን ለቀዋል።ጄቶዲያ ሥልጣን የለቀቁት የሚመሩት አማፂ ቡድን የቀድሞዉ የሐገሪቱን መንግሥት አስወግዶ ሥልጣን ከያዘ ወዲሕ ደሐይቱን አፍሪቃዊት ሐገር የሚያብጠዉን ግጭትና ሁከት መቆጣጠር አልቻሉም የሚል ወቀሳና ግፊት ከያለባቸዉ በኋላ ነዉ።ግፊቱን ካደረጉት ዋናዋ የቀድሞ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ እና የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ቢያዘምቱም ሠላም ማስፈን ግን አልቻሉም።ጄቶዲያ ንጃሚና ቻድ በተደረገዉ የማዕከላዊ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ECCAS) ጉባኤ ላይ ሥልጣን መልቀቃቸዉን ሲያዉጁ፥ የአዉሮጳ ሕብረት ደግሞ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማዝመት ማሰቡ ከብራስልስ ተሰምቷል።የሕብረቱን ዝግጅትና የሠራዊቱን ተልዕኮ በተመለከተ የብራስልሱን ወኪላችንን ገበያዉ ንጉሴን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ