1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማይተላለፉ በሽታዎች

ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2005

ከሰዉ ወደሰዉ የማይተላለፉ በሽታዎች ትኩረት እንደተነፈጋቸዉ የህክምና ባለሙያዎች አዘዉትረዉ ይጠቁማሉ። እንዲህም ሆኖ ከእነዚህ በሽታዎች መካከል በተለይ ኢትዮጵያ ዉስጥ የልብ ህመም፤ የደም ብዛት እንዲሁም የስኳር በሽታ ከፍተኛ ትኩረት ሲያገኙ ካንሰርን በሚመለከት ህብረተሰቡ ዝምታን እንደሚመርጥ ነዉ የሚነገረዉ።

https://p.dw.com/p/16mws
ምስል Frank Hajasch

የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለዉ በዓለም ከሚከሰተዉ ሞት 60 በመቶዉ የሚሆነዉ በህክምናዉ ባለሙያዎች አገላለፅ ነን ኮሙኒከብል ዲዚዝ ማለትም ከሰዉ ወደሰዉ በማይተላለፉ በሽታዎች ምክንያት ነዉ። ከእነዚህ በሽታዎች አንዱ ደግሞ ካንሰር ነዉ። ካንሰር ሲባል አስቀድሞ በሰዉ አእምሮ የሚከሰተዉ ያለመዳኑ ነገር ነዉ።

Deutschland Krebskranke Kinder im Krankenhaus
ጀርመን፤ የካንሰር ታማሚ ሕፃናትምስል picture-alliance/dpa

በሽታዉ እንዲህ ይታሰብ እንጂ ቀድመዉ ለህክምናዉ ከደረሱ ወገኖች አንዳንዶች ፍፁም እንደዳኑ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ አካላቸዉ ላይ ጉዳት ቢደርስም ነፍሳቸዉ ሳታልፍ ቀጣይ በርካታ ዘመናትን ከካንሰር ነፃ ሆነዉ ለመኖር እንደታደሉ ይታያል።

በየዓመቱ ጥቅምት ወር ሲመጣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስለጡት ካንሰር ሰዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ በየደረጃዉ የተለያዩ ዝግጅቶች ይከናወናሉ። ይህም ሆኖ ታዲያ ኢትዮጵያ ዉስጥ ኅብረተሰቡ ባጠቃላይ ለካንሰር ያለዉ ግምት ስጋትና ሀፍረት የተሞላበት ከመሆኑ በላይ በድብቅ መያዝን መምረጡ ጉዳቱን ሊያከፋዉ እንደሚችል የሚገምቱ ብዙዎች ናቸዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ