1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማይክል ሀኪም ክስና ቤተሰቦቹ

ረቡዕ፣ የካቲት 3 2002

ታዋቂው የፖፕ ሙዚቃ ንጉስ ማይክል ጃክሰን ሆን ተብሎ ተገድሏል ብለው እንደሚያምኑ ወላጅ አባቱ አስታወቁ ። በርሳቸው ዕምነት ሁሉ ነገር በሀኪሙ ላይ ተላከከ እንጂ ለማይክል ሞት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች ከጀርባ አሉ ።

https://p.dw.com/p/LyFT
ማይክል ጃክሰንምስል AP

በዶክተሩ ላይ ክስ የመሰረተው አቃቤ ህግ ግን ይህን መላምት የሚያረጋግጥ ማስረጃ የለውም ። ባለፈው ዓመት ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ ም ከዚህ ዓለም በሞት በተለየው በማይክል ጃክሰን የግል ሀኪም ላይ የተመሰረተው ክስ እንዳላረካቸው ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም ተናግረዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ