1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማይክል ጃክሰን ሞት ምክንያት መታወቅ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 19 2001

የተወዳጁ የዓለም የሙዚቃ ንጉስ የማይክል ጃክሰን ሞት ምክንያት ከልክ ያለፈ አደንዛዥ መድሀኒት መሆኑን የሎስ አንጀለስ ምርመራ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/JHp3
ምስል picture-alliance/ dpa

በምርመራው ጽህፈት ቤት ዘገባ መሰረት፡ ማይክል ጃክሰን በነበረበት የእንቅልፍ እጦት ሰበብ በግል ሀኪሙ በዶክተር ኮንራድ መሪ ከልክ በላይ በተሰጠው መድሀኒት ሞቶዋል። ጉዳዩ የነፍስ ግድያ ወንጀል ነው የሚል ማጠቃለያ ላይ መድረሱን ይፋ ያልሆኑ ዘገባዎች እያመላከቱ ነው።

አበበ ፈለቀ /አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ