1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል የእጅ ስልክ መጠለፍ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 14 2006

የጀርመን መራሂተ-መንግስት የእጅ ስልክ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የስለላ ተቋም ሳይጠለፍ አይቀርም መባሉ ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመንን እያነጋገረ ነው። ዋሽንግተን ሜርክል አልተሰለሉም፣ አይሰለሉምም ብላለች።

https://p.dw.com/p/1A5nb
ምስል imago/IPON

ከወራት በፊት በቀድሞው የአሜሪካ ሰላይ ኤድዋርድ ስኖውዳን በኩል ያፈተለከው ሚስጥራዊ ሠነድ የአሜሪካን መንግሥት እንደ ጀርመን ያሉ ወዳጆቹ የሆኑ መንግሥታትን እንደሚሰልል ይጠቅሳል። በወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ማስተባበያ መስጠቱም ይታወሳል። ይሁንና ጉዳዩ አሁንም እንደ አዲስ በመነሳት ላይ ነው።

ፈረንሣይ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የስልክ ጥሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የስለላ ተቋም ክትትል ተደርጎባቸዋል ስትል ፈረንሣይ በሳምንቱ መጀመሪያ፣ ሰኞ ዕለት ቅሬታዋን አሰምታለች። ንናንት ማምሻውን ደግሞ ከወደ ጀርመን የተሰማው ዜና ጉዳዩ የተወሳሰበ ሳይሆን እንደማይቀር አመላክቷል። የጀርመን መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የእጅ ስልክ በአሜሪካኖች ረቂቅ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ የስለላ ተግባር ሳይፈፀምበት እንዳልቀረ ነው የተነገረው። በእዚህ ጉዳይ ላይ የጀርመን መንግሥት አቋም ምንድን ነው ስል ነበር ለበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጥያቄ ያቀረብኩለት።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ