1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል ግብዣና መዘዙ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 20 2001

ሜርክል ለዶቸ ባንክ አገረ ገዢ ለዮሴፍ አከርማንን ሥልሳኛ አመት የልደት በአል ቅልጥ ያለ የራት ግብዣ ደግሰዉላቸዋል።በግብዣዉ ላይ ከሰላሳ የሚበልጡ ታዋቂ ባለሐብቶች፣ ባለሥልጣናትና ጋዜጠኞች ተገኝተዉ ነበር

https://p.dw.com/p/JIuS
ጋባዝና ተጋባዥምስል AP

የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የሐገሪቱን ትልቅ ባንክ አገረ-ገዢ የልደት በአልን ለማክበር በመንግሥት ወጪ መደገሳቸዉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ቁጣ ቀስቅሷል።ሜርክል ለዶቸ ባንክ አገረ ገዢ ለዮሴፍ አከርማንን ሥልሳኛ አመት የልደት በአል ቅልጥ ያለ የራት ግብዣ ደግሰዉላቸዋል።በግብዣዉ ላይ ከሰላሳ የሚበልጡ ታዋቂ ባለሐብቶች፣ ባለሥልጣናትና ጋዜጠኞች ተገኝተዉ ነበር።የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እንደሚሉት መራሒተ መንግሥቷ ሕዝብ በከፈለዉ ቀረጥ የግል እንግዳቸዉን ማስተናገዳቸዉ ሕገ-ወጥ ነዉ።ይልማ ሐይለ-ሚካኤል ከበርሊን ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ይልማ ሐይለ-ሚካኤል /ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ