1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል መስራች

ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2008

በአዲስ አበባ በርካታ አረጋውያንን እና የአዕምሮ ሕሙማንን በመርዳት ላይ የሚገኘው ወጣት ብንያም በለጠ «ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ ይበቃል» የሚል የሕይወት ፍልስፍና ይዞ እንደሚጓዝ ይናገራል።

https://p.dw.com/p/1GpNG
Pflegeheim in Addis Abeba Meqedonya
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የሜቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል መስራች

ወጣት ብንያም የከፈተው ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በአሁኑ ጊዜ እስከ 800 ሰዎች ለሚጠጉ ሰዎች ርዳታ ይሰጣል። ብንያም በለጠ በዶቼቬለ አድማጮች ጥቆማ ፣ በአካባቢያቸው በአርአያነት ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል፣ ከፍተኛውን ድምፅ በማግኘት በአንደኝነት ተመርጧል። የወጣት ብንያም በለጠ የሕይወት ተሞክሮ ምን ይመስላል? የአዲስ አበባ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ከወጣቱ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ