1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ አፍሪቃ ድርቅና የኦክስፋም ማስጠንቀቂያ

ረቡዕ፣ መስከረም 20 2002

ባሁኑ ወቅት ሰዎች የሚበሉ-የሚጠጡት የላቸዉም፥ ከብቶችም እየሞቱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/JurV
ከብቶች እየሞቱ ነዉምስል picture-alliance/ dpa

ምሥራቅ አፍሪቃን የመታዉ ድርቅ በአካባቢዉ የአስር አመት ታሪክ ደርሶ የማያዉቅ ሰብአዊ ቀዉስ ሊያስከትል እንደሚችል የብሪታንያዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት አስጠነቀቀ።ኦክስፋም እንደሚለዉ ሰባት ሐገራትን ክፉኛ የመታዉ ድርቅና ባካባቢዉ ካላባራዉ ግጭት ጋር ተዳምሮ ሃያ ሰወስት ሚሊዮን ሕዝብ ለረሐብ አጋልጧል።የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለለንደኑ ዘጋቢያችን ለድልነሳ ጌታነሕ እንደነገሩት ባሁኑ ወቅት ሰዎች የሚበሉ-የሚጠጡት የላቸዉም፥ ከብቶችም እየሞቱ ነዉ።

ድልነሳ ጌታነሕ/ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ