1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሩቃን ሥራ አጥነት እና የትምህርት ጥራት በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ሰኔ 27 2008

ከያዝነዉ ሳምንት ጀምሮ በሚቀጥሉት ወራት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ ዩኑቨርሲቲዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/1JIvg
Karte Äthiopien englisch

[No title]

እነዚህ ተመራቂዎች ያለፉበት የትምህርት ስርዓት በሥራው ዓለም ተፈላጊነታቸው ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው የመስኩ ባለሞያዎች ይናገራሉ ። ይህም ምሩቃን የስራ ገበያ ዉስጥ ለመግባት ትልቅ ፈተና እንደሆነባቸዉ እና በአገሪቱ ለሚታየው ስራ አጥነት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉም ይከራከራሉ ። የሴሜን ሸዋው ነዋሪ ዳንኤል በላቸዉ ይህን ሃሳብ ከሚጋሩት አንዱ ነው ።ከስድስት ዓመት በፊት በአፕላይድ ፊዚክስ ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ቢመረቅም ስራ ስላላገኘ ወደ ንግድ ገባሁ ይላል።


በ2000 ዓም ከጅማ ዩኒቨርስቲ በጅኦግራፍ መምህርነት የተመረቁት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪ መምህር ዩሱፍ ኑርዬ በመንግሥት ትምህርት ቤት ውስጥ ያስተምራሉ ። ከ6 ዓመት ገደማ አንስቶ መንግስት መምህራኖቹን ካስመረቀ በኋላ ራሳቸዉ ሥራ ይፈልጉ መባሉ የብዙ መምህራን ስራ አጥነት መንስኤ መሆኑን ይናገራሉ።


አብዛኛው ምሩቅ የመንግሥት ሥራ ያገኛል ማለት አይደለም የሚሉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ የመምህራንን ቅጥር በተመለከተ ለዉጥ ተደርገዋል ይላሉ።

መንግስት 11 ተጨማሪ ዩኒቨርስቲዎችን ለመገንባት እቅድ ማዉጣቱ እየተዘገበ ነው። እንደ ዩሱፍ ያሉ አስተያየት ሰጭዎች « መንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚገነባውም ሆነ ተማሪዎችን የሚያስመርቀው <<ለቁጥር ወይም ለይስሙላ>> እንጅ ተመርቀው ስራ ያገኛሉ ወይም አገር ይረካባሉ የሚለዉን ታሳቢ አድርጎም አይደለም ይላሉ ። ዶክተር ካባ ግን በዚህ አይስማሙም ።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ