1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ዘመቻና የመድረክ ወቀሳ

ዓርብ፣ መጋቢት 4 2007

የመድረክ ባለሥልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አባላቶቻቸዉን የሚያስሩ፤ የሚደበድቡና የሚያንገላቱት የየአካባቢዉ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1EqVU
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) በቅርቡ በሚደረገዉ ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎቹና ምርጫዉን የሚያስፈፅሙ አባላቱ በየአካባቢዉ እየታሰሩ፤ እየተደበደቡና እየተንገላቱ ነዉ በማለት ወቀሰ። የመድረክ ባለሥልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አባላቶቻቸዉን የሚያስሩ፤ የሚደበድቡና የሚያንገላቱት የየአካባቢዉ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ናቸዉ። በደሉን ለማስቆም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁነኛ እርምጃ እንዲወስድ ባለሥልጣናቱ ጠይቀዋል።መድረክ ለምርጫዉ ያዘጋጀዉን የመወዳደሪያ ማንፌስቶም ይፋ አድርጓል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ