1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምስጋና ቀን አከባበር እና ኢትዮጽያዉያን በአሜሪካ

ሐሙስ፣ ኅዳር 14 2004

በጎርጎረሳዉያኑ ህዳር ወር አራተኛ ሳምንት ሃሙስ እለት በሰሜን አሜሪካ የሚከበረዉ Thanksgiving Day ማለት የምስጋና ቀን ብሄራዊ በአል ነዉ።

https://p.dw.com/p/RyI2
ምስል picture-alliance / dpa / Stockfood


በጎርጎረሳዉያኑ ህዳር ወር አራተኛ ሳምንት ሃሙስ እለት በሰሜን አሜሪካ የሚከበረዉ Thanksgiving Day ማለት የምስጋና ቀን ብሄራዊ በአል ነዉ። ይኸዉ እለት ቤተሰብ ጓደኛ የሚገናኝበት በቤተሰብ በአልነቱም ይታወቃል። በአመት ዉስጥ ተራርቆ ያለ ቤተሰብ ጓደኛ ከአለበት የሚሰባሰብበት በተለይ በጋራ እራት የሚበላበት በአልም እንደሆነ ጽሁፎች ይጠቁማሉ። ይህ በአል ሲዳረስ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ አዉራጎዳናዎች እና የአየር ማረፍያዎች በተጓዦች ይጨናነቃሉ። በአሉ እለት በተለይ የዳክዪ ጥብስ የድንች ስኳር እና የድፍን ባቄላ አደንጓሪ ወጥ በአሜሪካዉያኑ የምግብ ጠረቤዛ ላይ ይቀርባል። ይህ ባህል የመጣዉ በጥንት ግዜ አዉሮጻዉያን ወደ አሜሪካ ፈልሰዉ ሲገቡ ሪድ ኢንድያንስ የሚሉዋቸዉ ነባር አሜሪካዉያን መራባቸዉን አይተዉ ይህንን አይነት ምግብ ስላቀረቡላቸዉ እንደነበር ታሪክ ያሳያል።በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጽያዉያን የምስጋናንን ቀን ቡና አፍልተዉ ዳቦ ደፍተዉ ነዉ እንደባህላቸዉ እንኳን አደረስ አደረሽ የሚባባሉት። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝዉ የኢትዮጽያ ህብረተሰብ አገልግሎት የልማት ማህበር በበኩሉ ላለፉት ስምንት አመታት ይህንን በአል ያከብር የነበረዉ በዋሽንግተን እና አካባቢዉ ቤት አልባ ኢትዮጽያዉያንን በማሰባሰብ ነበር። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

Obama begnadigt Truthahn
ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ በምስጋና ቀን ከቀረበላቸዉ ዳክዪ ጋርምስል AP


አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ