1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምቤኪ ትንሳኤና ዉድቀት

ማክሰኞ፣ መስከረም 13 2001

ብዙዎቹ የአፍሪቃ አቻዎቻቸዉ እንደሚያደርጉት ተቀናቃኞቻቸዉን ለማሰር፥ ለማጥፋት፥ ሥልጣናቸዉን በጠመንጃ ለማስከበር አልሞከሩም።የሐምሳ-ሁለት ዘመን ታጋይ ናቸዉ ጀግና።በጀግንነታቸዉ ያገኙትን ሥልጣን በጀግንነት በሰላም ለቀቁት

https://p.dw.com/p/FMx7
ምቤኪምስል AP
ኔሬሬ፥ ሴንጎር፥ ማንዴላ፥ ቺሳኖ ለብዙ ጊዜ ታግለዉ የያዙትን ሥልጣን በፈቃዳቸዉ ለቀዋል።አንዳቸዉም ግን በፓርቲያቸዉ ወይም በተቃዋሚዎቻቸዉ ግፊት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ሳበቃ ሥልጣናቸዉን አላስረከቡም። ለአፍሪቃዉያን ነፃነት፥ እኩልነት የተዋጉ የታገሉ፥ የተሟገቱት ምቤኪ ማንም አፍሪቃዊ መሪ አድርጎት የማያዉቀዉን ትናንት አደረጉት።አስተምሕሮታቸዉ ነዉ-ናፋቂዊ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።