1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ለጋምብያ የጀመሩት ጥረት 

ማክሰኞ፣ ጥር 2 2009

በናይጀሪያ ፕሬዚደንት መሃማዱ ቡሃሪ የሚመራ አንድ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የልዑካን ቡድን በጋምቢያ የተፈጠረውን ቀዉስ ለመሸምገልና መስመር ለማስያዝና የጀመረውን ጥረት እንደቀጠለ ነዉ።  

https://p.dw.com/p/2VaF1
Gambia Yahya Jammeh in Banjul
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Delay

በናይጀሪያ ፕሬዚደንት መሃማዱ ቡሃሪ የሚመራ አንድ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የልዑካን ቡድን በጋምቢያ የተፈጠረውን ቀዉስ ለመሸምገልና መስመር ለማስያዝና የጀመረውን ጥረት እንደቀጠለ ነዉ።  ይኸው የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የኤኮኖሚ ማህበረሰብ፣ በምህፃሩ የ«ኤኮዋስ» የልዑካን ቡድን ነገ ረቡዕ ወደ ጋምቢያ መዲና ባንጁል በማቅናት በምርጫ የተሸነፉትን ፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜህን  ስልጣኑን ለምርጫዉ አሸናፊ እንዲያስረክቡ ለማግባባት እንደሚሞክር ተገልጾዋል። ያህያ ጃሜ ስልጣኑን አላስረክብም ብለዉ አሻፈረኝ ካሉ ግን በጦር ኃይል ለማስገደድ የተነደፈዉ እቅድ ስራ ላይ እንደሚዉል ከወዲሁ በደብዳቤ ጃሜን አስጠንቅቀዋል። ባለፈዉ ሕዳር መጨረሻ ላይ በጋምቢያ በተካሄደዉ ምርጫ የተሸነፉት ፕሬዝደንት ያህያ ጃሜህ መጀመሪያ ላይ የምርጫዉን ዉጤት ከተቀበሉ በኋላ ዳግም መሻራቸዉ ይታወቃል። ዝርዝሩን የበርሊኑ ወኪላችን ልኮልናል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል 
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ