1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራብ አፍሪቃ ችግርና ኤኮዋስ

ዓርብ፣ ግንቦት 22 2006

የናጄሪያዉ ቦኮ ሐራም፤ የማሊ ነዉጠኞች፤ በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሱ የባሕር ወንበዴዎችንም ሆነ ሌሎች «ሠላም አዋኪ» ያሏቸዉ ሐይላትን ጥቃት ለመቋቋም የማሕበረሰቡ አባላት ብቻቸዉን አይችሉትም

https://p.dw.com/p/1C9g9
ምስል DW/G. Tedla

የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ ECOWAS-በእንግሊዝኛ ምፃሩ በአባል ሐገራት የተከሰቱ የሠላምና የፀጥታ መታወኮችን ለማስወገድ የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብን ትብብርና ድጋፍ ጠየቀ። የማሕበረሰቡ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ቶጋ ጋየንግ ማኪንቶሽ አዲስ አበባ ዉስጥ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የናጄሪያዉ ቦኮ ሐራም፤ የማሊ ነዉጠኞች፤ በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሱ የባሕር ወንበዴዎችንም ሆነ ሌሎች «ሠላም አዋኪ» ያሏቸዉ ሐይላትን ጥቃት ለመቋቋም የማሕበረሰቡ አባላት ብቻቸዉን አይችሉትም።በዚሕም ምክንያት ምክትል ፕሬዝዳናቱ እንደሚሉት ችግሮቹን ለማስወገድ የመላዉ አፍሪቃና የተቀረዉ ዓለም ትብብር አስፈላጊ ነዉ።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ