1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ እጥረትና የረሃብ ስጋት በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥር 8 2008

የረሃብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የተባለው ድርጅት እንዳስታወቀው ደግሞ ለጋሽ ሃገራት ለድርቁ መቋቋሚያ እንዲሰጡ ከተጠየቁት እርዳታ ፣የተገኘው ልገሳ አነስተኛ በመሆኑ ሁኔታዎች ተባብሰው ወደ ረሃብ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

https://p.dw.com/p/1HeS0
Dürre – Äthiopien
ምስል European Commission DG ECHO / CC BY-SA 2.0

የምግብ እጥረትና የረሃብ ስጋት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ለምግብ እጥረት የሚዳርገው ህዝብ ቁጥር ከዚህ ቀደም ከተሰጠው ግምት በላይ እንደሚሆን ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው ። እነዚሁ በመስኩ የተሰማሩ ድርቶች እንደሚሉት በጎርጎሮሳዊው 2016 ፣ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ ቁጥር እስከ 15 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል ። የረሃብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የተባለው ድርጅት እንዳስታወቀው ደግሞ ለጋሽ ሃገራት ለድርቁ መቋቋሚያ እንዲሰጡ ከተጠየቁት እርዳታ ፣የተገኘው ልገሳ አነስተኛ በመሆኑ ሁኔታዎች ተባብሰው ወደ ረሃብ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። የምግብ እጥረት እና የረሃብ ስጋት በኢትዮጵያ የውይይቱ ርዕስ ነው ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ