1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞሪሽየስ እና የአውሮጳ ህብረት ስምምነት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 27 2005

ደሴቲቱ ሞሪሽየስ 35 ሶማልያውያን የባህር ወንበዴዎችን በሀገሯ ለማሰርና ለፍርድ ለማቅረብ ዝግጁ መሆንዋን አስታወቀች። የሞሪሽየስ መንግሥት ይህን ስምምነቱን ሰሞኑን ከአውሮጳ ህብረት ጋ በተፈራራረመው ውል አረጋግጦዋል።

https://p.dw.com/p/16c87
ARCHIV - Ein somalischer Pirat steht vor der Küste von Hobyo, Somalia, Wache (Archivfoto vom 23.10.2008). Angesichts der zunehmenden Überfälle auf Schiffe vor der Küste Somalias ermächtigte der Weltsicherheitsrat am 02.06.2008 die UN-Mitgliedsstaaten, auch in den somalischen Hoheitsgewässern gegen Piraten vorzugehen. Mitte November waren in Somalia 17 Schiffe und rund 340 Seeleute in der Gewalt der Seeräuber. Am 15. November kaperten Piraten den 330 Meter langen saudischen Öltanker «Sirius Star». Die Ladung: zwei Millionen Barrel Öl mit einem Marktwert von umgerechnet gut 79 Millionen Euro. EPA/BADRI MEDIA (zu dpa-Paket: "Jahreswechsel" vom 03.12.2008) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture alliance / dpa

የአውሮጳ ህብረት የሞሪሸየስ መንግሥት በቁጥጥር የዋሉትን የባህር ወንበዴዎች ለሚቀበልበት፡ እንዲሁም፡ በወህኒ አቆይቶ ፍርድ ፊት ለሚያቀርብበት ስምምነቱ ሦስት ሚልዮን ዩሮ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ይኸው የሞሪሸየስ መንግሥት ውሳኔ ያልደገፉት በሀገሪቱ የሚገኙት ሲቭል ማህበረሰብ አባላት መንግሥት ይህን ርምጃ የወሰደበትን ምክንያት ማጠያየቅ ይዘዋል።
ሞሪሽየስ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እያወከ ያለውን የባህር ላይ ውንብድና ሞሪሽየስ ተመልካች በመሆን ልታሳልፈው እንደማይገባ የሀገሪቱ መንግሥት ይናገራል። የሞሪሽየስ መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር ናቪን ራምጉላም እንዳስረዱት፡ በሕንድ ውቅያኖስ የሚፈፀመው የባህር ላይ ውንብድና ሞሪሽየስ በባህሩ መሥመር ወደ ሀገሯ በምታስገባው እና ከሀገሯ በምትልከው ንግድ፡ እንዲሁም፡ በዋነኞቹ የሀገሪቱ የኤኮኖሚ ምሰሶ በሆኑት በአሣ ማስገሩ እና በቱሪዝሙ ዘርፎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፎዋል። በመሆኑም፡ ሀገራቸው የባህር ላይ ወንበዴዎችን እሥርና ፍርድን በተመለከተ ከአውሮጳ ህብረት ጋ የደረሰችውን ስምምነት ትክክለኛ ነው ሲሉ ለሀገራቸው ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። 
« ይኸው ክስተት እጅግ ትልቅ ደረጃ ላይ በመድረሱ አንዲት ሀገር ብቻዋን ልታሸንፈው አትችልም። የባህር ላይ ወንበዴዎችን ከዚሁ ተግባራቸው ለማከላከል በአንፃራቸው ጠንካራ ክትትል ማድረጉ አንዱ ዋነኛ ዘዴ ነው። አንዳንድ ተይዘው የነበሩ የባህር ወንበዴዎች በፃ ሲለቀቁ አይተናል። በዚህም የተነሳ ነው በኤኮኖሚያችንም ላይ ጉዳት ስለሚያደርሱ በአንፃራቸው ቀጣይ ክትትል እንዲደረግ ከአውሮጳ ህብረት ጋ ስምምነት የተፈራረምነው። ህብረቱ እሥረኞቹን የምንቀበልበትን እና ለፍርድ የምናቀርብበትን፡ እንዲሁም፡ አንድ ወህኒ ቤት እና አዲስ ፍርድ ቤት የሚሰራበትን ወጪ ይሸፍናል። »
የመጀመሪያው የባህር ወንበዴዎቹ ችሎት መቼ እንደሚጀመር ገና ቀን አልተቆረጠም። እርግጥ ብዙው የሞሪሽየስ ሕዝብ በዚህ ጉዳይ ላይ የሀገሩ መንግሥት በወሰደው ውሳኔ ላይ ጣልቃ አልገባም። ግን፡ የአንድ ሲቪል ማህበረሰብ አባል የሆኑት አሾክ ሱብሮን የመንግሥቱ ውሳኔ ትክክለኟ እንዳልሆነ ነው ያመለከቱት።
« የሞሪሽየስ መንግሥት በሚገባ ሳያጤን ነው ይህን ውሳኔ የወሰደው።  በኛ አካባቢ ብዙ ግዛቶች ያሉት የአውሮጳ ህብረት የባህር ወንበዴዎቹን ችሎት ለምን በሞሪሽየስ ደሴት ለማካሄድ መወሰኑ አስገርሞኛል። በተለይ በሶማልያ የባህር ጠረፍ አካባቢ ለተስፋፋው የባህር ላይ ውንብድና ተጠያቂዎቹ ያካባቢውን የአሣ እና በባህሩ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት የሚበዘብዙት አውሮጳውያኑ መርከቦች መሆናቸው ሲታሰብ፡ ሕዝባችንን በማይመለከተው በዚሁ ጉዳይ ሰበብ ደሴታችንን አስጊ ሁኔታ ላይ መጣል አስፈላጊ አይደለም። » 
ዓለም አቀፉ የባህር ላይ ጉዞ ተከታታይ ጽሕፈት ቤት እንደሚገምተው ግን፡ የባህር ላይ ውንብድና እየቀነሰ በመሄዱ የባህር ወንበዴዎች ወደፊት በሞሪሽየስ ደሴት እንዲታሰሩ እና ችሎታቸውም በዚያ እንዲካሄድ ከአውሮጳ ህብረት ጋ የተደረሰው ስምምነት ጊዚያዊ ነው የሚሆነው። በ 2012 ዓም የመጀመሪያው አጋማሽ 69 የባህር ላይ ወንበዴዎች መያዛቸው ሲመዘገብ አምና በዚሁ ጊዜ  የተያዙት 163 ነበሩ። የባህር ላይ ውንብድና ለቀነሰበት ድርጊት፡ እንደ ዓለም አቀፉ የባህር ላይ ጉዞ ተከታታይ ጽሕፈት ቤት አስተያየት፡ መርከቦች በታጠቁ የፀጥታ ቡድኖች ከለላ ማግኘት የጀመሩበት አሰራር ነው።
 

ARCHIV - Im Rahmen der EU-Mission «Atalanta» hat die französische Marine am 03.05.2009 vor der ostafrikanischen Küste elf mutmaßliche Piraten gefangen genommen (Foto des französischen Verteidigungsministeriums). Am Horn von Afrika blüht die Seeräuberei. Das zwingt die EU dazu, neue Wege zu gehen. So soll die EU-Mission «Atalanta» Piraten auch am Strand angreifen dürfen. Foto: Französisches Verteidigungsministerium dpa
ምስል picture-alliance/dpa
Prime Minister of Mauritius Navinchandra Ramgoolam speaks at the 66th United Nations General Assembly at U.N. headquarters, Saturday, Sept. 24, 2011. (AP Photo/John Minchillo)
የሞሪሽየስ ጠቅላይ ሚንስትር ናቪን ራምጉላምምስል AP

አርያም ተክሌ
መሥፍን መኮንን