1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞሪታንያ ፕሬዚደንት ተተኩሶባቸው ቆሰሉ

እሑድ፣ ጥቅምት 4 2005

የሞሪታንያ ፕሬዚደንት ኡልድ አብደል አዚዝ ትናንት በመዲናይቱ ኑዋክሾት በአጀብ እየተጓዙ ሳለ ወታደሮች የፕሬዚደንቱ አጀብ መሆኑን ካለማወቅ በከፈቱት ተኩስ እጃቸው ላይ ከቆሰሉ በኋላ ዛሬ ለሕክምና ወደ ፓሪስ ፈረንሳይ መሄዳቸው ተነገረ።

https://p.dw.com/p/16PrR
Mauritania's President Mohamed Ould Abdel Aziz takes part in the closing news conference after a summit of Mediterranean neighbours at Verdala Palace outside Valletta, in this October 6, 2012 file photo. Abdel Aziz is undergoing treatment for a gunshot wound in a military hospital in the capital Nouakchott, a source at the presidency and two military sources told Reuters on October 13. They said Abdel Aziz was travelling by road when the incident occurred, but they did not give any further details. Security forces blocked roads leading to the hospital, witnesses said. REUTERS/Darrin Zammit Lupi/Files (MALTA - Tags: POLITICS BUSINESS HEADSHOT)
ምስል Reuters



በዚያ ከተደረገላቸው ቀዶ ጥገና በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ፕሬዚደንቱ ለሕዝባቸው ከፓሪስ ሐኪም ቤት አልጋቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።  ፕሬዚደንት አብደል አዚዝ የደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ለሕይወታቸው አስጊ አለመሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ሚንስትርም በቴሌቪዥን ገልጸዋል። ሚንስትሩ አክለው እንዳስረዱት፡ የሞሪታንያ ክብር ዘብ በስህተት በፕሬዚደንታዊው የተሽከርካሪዎች አጀብ ላይ ተኩሶዋል። ይሁንና፡ አደጋውን በተመለከተ የተለያየ ታሪክ ስለሚሰማ የሆነውን በትክክል ማወቁ በወቅቱ አዳጋች መሆኑን ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ቀደም ሲል አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የጦር መኮንን በሰጡት መግለጫ ፕሬዚደንቱ በአንድ በሞተር ባይስክል ይጓዝ በነበረ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በሰሜናዊ ኑዋክሾት እንደተተኮሰባቸው አስታውቀዋል።

አርያም ተክሌ
ልደት አበበ