1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሥልጣን ሽግግር ታሪክ በኢትዮጵያ፣

እሑድ፣ ግንቦት 15 2002

እጅግ ጥንታዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ፣ ከ 1928-1933፣ ለ 5 ዓመታት ከፋሺስት ኢጣልያ ወራሪ ሠራዊት ጋር ተጋፍጣ፣ ሙሉ ነጻነቷን መልሳ በእጇ ለማስገባት መሪር ትግል

https://p.dw.com/p/NVLi
ምስል AP

ከማካሄዷ በስተቀር፣ በተለይ መሃል ግዛቷን አንድም የውጭ ኃይል ተቆጣጥሮት አያውቅም።

ሰፊውን ግዛቷን፣ ነግሥታት ፣ መሣፍንት፣ ሡልጣኖች፣ አሚሮች ተከፋፍልው ቢገዙም፣ አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ሥር የኖረች ሀገር ናት።

Portraitbild von Äthiopiens Ex-Diktator Mengistu Haile Mariam
ምስል picture alliance/dpa

ኢትዮጵያ ፣ የዘመኑ ሥልጣኔና አስተዳደር መዓዛ ከሸተታት፤ ከአንድ መቶ ዓመት በላይ አስቆጥሯል። ያም ሆኖ፣ የተለያየ ስያሜ ይሰጠው እንጂ፣ የአስተዳደር ስልቱ መሠረታዊ ለውጥ አልታየበትም። ኢትዮጵያውያን ፣ እንደ ንብረት ውርስ፣ በትውልድ ሥልጣን በሚተላለፍለት ግለሰብ፣ በሚሾም፣ ወይም በጉልበት ሥልጣን በሚጨብጥ መሪ መገዛት እንጂ፣ ህዝብ፣ በትክክል በሚመርጠው መሪ፣ የመተዳደር ዕድል አጋጥሞአቸው አያውቅም። በታሪኳ፣ በብዙ ጉዳዮች፣ ቀዳሚውን ቦታ የያዘችው ሀገር፣ በዚህ ረገድ በመጨረሻው ረድፍ ከተሰለፉት መካከል ሆኗል የምትደመረው።

Äthiopien Meles Zenawi
ምስል AP

በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ፣ የባዕድን ተጽእኖ የመከላከል የነጻነት ታሪክ፣ በህዝብ የሚመረጥ መንግሥት ለመመሥረት ያደጋተበት ምክንያት ምንድን ነው? በዩናይትድ እስቴትስ፣ ቨርጅኒያ ውስጥ፣ የክሪስቶፈር ንው ፖርት ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር፣ ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ፤

(ድምፅ)---------------

በምዕራቡ ዓለም እንደሚታየው ለቡድን ነጻነት መሠረት የሆነውን ፣ የግለሰቦችን ነጻነት ያጎናጸፈውን ፤ መሠረታዊ የዴሞካራሲ ሥርዓት ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመትከል ማን ያህል ጊዜ ይወስድ ይሆን?!

------(ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ)---

ምርጫ 1997

የምዕራቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በአብዛኛው አለም በተንሠረፋበት በቅርቡ ዘመንም ኢትዮጵያውያን በፍላጎታቸው መሪዎቻቸውን ለመምረጥ ሞክረው ነበር ።

An Ethiopian woman
ምስል AP

ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ሶስት ሙከራዎች በአንፃራዊ መመዘኛ የተሻለው የ 1997 ምርጫ ነበር ። ውጤቱና መዘዙ ግን የነበረውን ተስፋ ሁሉ አጨናጉሎታል ። መሳይ መኮንን የዚያን ጊዜውን እውነታ በአጭሩ ይቃኘዋል ።

Äthopien Unruhen Demonstranten in der Nähe von Addis Abeba
ምስል AP

ተክሌ የኋላ

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ