1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩሲያና የጆርጂያ ዉዝግብ፥ የፑቲን ጉብኝት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 7 2001

ፑቲን አብኻዚያን የጎበኙት ሩሲያና ጆርጅያ ከቲቢሊሲ መአከላዊ መንግሥት አስተዳደር በተገነጠሉት ሁለት ግዛቶች ሰበብ የገጠሙት ጦርነት አንደኛ አመት በታሰበ ማግሥት መሆኑ ነዉ።

https://p.dw.com/p/J9Ae
የሱኩሁሚ ነዋሪዎች ፑቲንን ሲቀበሉምስል AP

የሩሲያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ቭላድሚር ፑቲን ከጆርጅያ ተገንጥለዉ ነፃነታቸዉን ካወጁት ሁለት አወዛጋቢ ግዛቶች መካካል አብኻዚያን ትናንት መጎብኘታቸዉ በሞስኮና በቲቢሊሲ መካካል ያለዉን ዉዝግብ እንዳዲስ አንሮታል።ፑቲን አብኻዚያን የጎበኙት ሩሲያና ጆርጅያ ከቲቢሊሲ መአከላዊ መንግሥት አስተዳደር በተገነጠሉት ሁለት ግዛቶች ሰበብ የገጠሙት ጦርነት አንደኛ አመት በታሰበ ማግሥት መሆኑ ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትር ፑቲን በትናንቱ ጉብኝታቸዉ «ነፃ ሐገር ላልዋት» ለአብኻዚያ ሞስኮ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገብተዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንግሤ/ነጋሽ መሐመድ/ሸዋዬ ለገሠ