1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩስያ ባህር ኃይል እና የዩክሬይን ስምምነት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 20 2002

በሩስያ እና በዩክሬይን መካከል የተደረሰው አከራካሪው የጦር ኃይል እና የኃይል ምንጭ ስምምነት በሁለቱ ሀገሮች ምክር ቤቶች ጸደቀ።

https://p.dw.com/p/N8k0
የዩክሬይን እንደራሴዎች ሲደባደቡምስል AP

በስምምነቱ መሰረት፡ በክሬሚያ አካባቢ በጥቁር ባህር የሚገኘው የሩስያ ባህር ኃይል በዚያ ቢያንስ ሀያ አምስት ዓመት እንዲቆይ ተወስኗል። በምላሹ ክስረት አፋፍ ላይ የምትገኘዋ ዩክሬይን ከሩስያ በምትገዛው ጋዝ ላይ ሰላሳ ከመቶ ቅናሽ ታገኛለች። ስምምነቱን የተቃወሙት የዩክሬይን ምክር ቤት እንደራሴዎች በድምጽ አሰጣጡ ወቅት ሲሰዳደቡ፡ በእንቁላል ሲደባደቡ እና በጢስ ቦምብ ሲታጠኑ ታይተዋል።

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ