1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርዋንዳ የጦር ወንጀለኞች እና የተበየናቸው የዕድሜ ልክ እስራት ቅጣት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2001

በአሩሻ ታንዛንያ የሚገኘው የተመ የርዋንዳን የዘር ማጥፋት ወንጀል ጉዳይን የሚመለከተዉ የጦር ወንጀል ችሎት ከሁለት ቀናት በፊት በቀድሞዉ ወታደራዊ ጀነራል ቴዎኔስቴ ቦጎሶራና በሶስት የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት ፈረደ።

https://p.dw.com/p/GJzc
የቀድሞ ወታደራዊ ጀነራል ቴዎኔስቴ ቦጎሶራና
የቀድሞ ወታደራዊ ጀነራል ቴዎኔስቴ ቦጎሶራናምስል AP

የቀድሞዎቹ የሩዋንዳ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሀገሪቱ እአአ በ 1994 ዓም በቱትሲዎችና በለዘብተኛ ሁቱዎች አንጻር የተፈፀመዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል በማቀነባበር የተከሰሱ ሲሆን፡ ካለፉት አስራ አንድ ዓመታት ወዲህ በእስራት ላይ የሚገኙት ቦጎሶራ ባቀነባበሩት ጭፍጨፋ በዚያን ጊዜ ወደ ስምንት መቶ ሺህ ሰው ነበር የተገደሉት።