1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሮማዉ ርዕሠ-ሊቀ ጳጳስ ጉብኝት በመካከለኛዉ ምሥራቅ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2001

ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዚሕ ቀደም በሰጧቸዉ አስተያየቶችና በወሰዷቸዉ እርምጃዎች ምክንያት ጉብኝታቸዉን አረቦችም አይሁዶችም በጥሩ ስሜት የሚቀበሉት አይመስሉም።

https://p.dw.com/p/HmDQ
ቤኔድክት 16ኛ እና ንጉስ አብደላሕምስል AP

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ መካከለኛዉ ምሥራቅን ለመጎብኘት ዛሬ አማን-ዮርዳኖስ ገብተዋል።የቫቲካን ባለሥልጣኖች እንደሚሉት የካቶሊኮቹ መንፈሳዊ አባት በአይሁድ፥ በክርስትና እና በእስልምና ሐይማኖቶች ቅዱስ ሥፍራዎች የሚያደርጉት ጉብኝት አለማ የሠላም፥ የእርቅና የፍቅር መልዕክትን ማስተላለፍ ነዉ።ይሁንና የየሩሳሌሙ ወኪላችን ዜናነሕ መኮንን እንደዘገበዉ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዚሕ ቀደም በሰጧቸዉ አስተያየቶችና በወሰዷቸዉ እርምጃዎች ምክንያት ጉብኝታቸዉን አረቦችም አይሁዶችም በጥሩ ስሜት የሚቀበሉት አይመስሉም።

ዜናነሕ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ