1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰመጉና የኢሕባሴማ የፍርድ ቤት ዉሎ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2005

የኢትዮጵያ መንግሥት የዛሬ ሰወስት ዓመት ግድም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሕበራት አዲስ ባፀደቀዉ ደንብ መሠረት ሁለቱ ተቋማት በድምሩ ከአስራ-ስድስት ሚሊዮን በላይ ብር ታግዶባቸዋል።ማሕበራቱ ገንዘቡ እንዲለቀቅላቸዉ እየተሟገቱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/16R0R
Der Gerechtigkeitsbrunnen (auch Justitiabrunnen) ist ein Figurenbrunnen in Frankfurt am Main. Brunnen der Justitia auf dem Römerberg ist die Göttin Justitia, der im Gegensatz zu den meisten anderen Darstellungen nicht die Augen verbunden sind. Der Brunnen steht in der Mitte des zentralen Römerbergs vor dem Rathaus. - Weiter wikipedia 24951989 liveostockimages - Fotolia 2010
ምስል Fotolia/liveostockimages

የኢትዮጵያ የፌደራል ሠበር ሠሚ ችሎት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤና የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር ባቀረቡት ይግባኝ ላይ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለፊታችን አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጠ።የኢትዮጵያ መንግሥት የዛሬ ሰወስት ዓመት ግድም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሕበራት አዲስ ባፀደቀዉ ደንብ መሠረት ሁለቱ ተቋማት በድምሩ ከአስራ-ስድስት ሚሊዮን በላይ ብር ታግዶባቸዋል።ማሕበራቱ ገንዘቡ እንዲለቀቅላቸዉ እየተሟገቱ ነዉ።ችሎቱ ከዚሕ ቀደም ዛሬ የመጨረሻ ብይን እንደሚሰጥ አስታዉቆ ነበር።ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት የወሰነዉ ግን በተለይ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር ጉዳዩን በድርድር ለመፍታት መጠየቁን በማስታወቁ ነዉ።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ካዲስ አበባ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ