የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ትምህርት ቤት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 30 2006ማስታወቂያ
የዛሬ 78 ዓም በፋሺሽት በኢጣልያ ወረራ ወቅት በፋሺሽቶች የተረሸኑት አቡነ ጴጥሮስ በተወለዱበት በፍቼ ከተማ በስማቸው የመታሰቢያ የሕፃናት ማሳደጊያና ትምሕርት ቤት በመሠራት ላይ ነው። ትምሕርት ቤቱን የምታሠራው ለሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት ያቆመችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ በፋሺሽት ኢጣልያ የተረሸኑት ሐምሌ 22 1928 ዓም ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰማዕቱን የአቡነ ጴጥሮስን ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና ግንዛቤ ለማስጨበጭ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀችው መድረክ ላይ የተገኘው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ