1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 20 2007

ባለሥልጣናቱ አክለዉ እንዳሉት የታሠሩ አባላቶቻቸዉን ለማስለቀቅና በፓርቲዉ ላይ ተከፈተ ያሉትን የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለማስወገድ ፓርቲዉ በፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል።

https://p.dw.com/p/1FGTA
Äthiopien Addis Abeba Blue Party
ምስል DW/G. Tedla

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር፤ሠማያዊ ፓርቲ፤ የሐገሪቱ መንግሥት በትንሽ በትልቁ «ሥሜን እያጠፋዉ ነዉ» በማለት ወቀሰ።የፓርቲዉ ባለሥልጣናት ዛሬ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ መንግሥት የፓርቲዉን አባላትና ባለሥልጣናት «አላግባብ አስሮብናል» ብለዋልም።ባለሥልጣናቱ አክለዉ እንዳሉት የታሠሩ አባላቶቻቸዉን ለማስለቀቅና በፓርቲዉ ላይ ተከፈተ ያሉትን የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለማስወገድ ፓርቲዉ በፍርድ ቤት ክስ ይመሰርታል።የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ባለፈዉ ሳምንት ሊቢያ ዉስጥ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያንን ለመዘከር አዲስ አበባ ዉስጥ የተደረገዉን የአደባባይ ሠልፍ አብጧል በማለት ፓርቲዉን ወቅሰዉት ነበር።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎታል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ