1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 2 2009

የየፓርቲዉ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ በስልክ እንደገለፁት አንድ የአመራር አባል እና አምስት አባላቱ የታሰሩበት ምክንያት በዉል አይታወቅም።

https://p.dw.com/p/2RAPA
Demonstration der Semayawi-Partei in Addis Ababa Äthiopien 22.09.2013
ምስል DW

BLue Party - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ በርካታ የብሔራዊ ምክር ቤት እና የፓርቲዉ አባላት በመንግሥት ፀጥታ ኃይላት መታሰራቸዉን አስታወቀ።የፓርቲዉ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ወዲሕ የፓርቲዉን መሪዎች ጨምሮ ከታሰሩት አባላቱ መካከል እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት የቀረቡት አንዱ ብቻ ናቸዉ። የፓርቲዉ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ በስልክ እንደገለፁት አባላቱ የታሰሩበት ምክንያት በዉል አይታወቅም። ፀሐይ ጫኔ አቶ ይድነቃቸዉን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ